Mr Tefera Barasa

አቶ ተፈራ ባራሳ

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ጀነራል ዳይሬክተር መልዕክት


ለአንድ ሀገር እድገት የኢኖቬሽናል ቴክኖሎጂ ሚና በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ ስለሆነም ቴክኖሎጂ መነሻ ያደረጉ የኢኖቬሽን ልማት ላይ ጠንክረን መስራት ይጠበቅበረናል፡፡
ከዘረፉ ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የባለድረሻ አካላትን ለይተን እየሰራን ቆይተናል፡፡ በመሆኑም ዉጥኑን ከግብ ለማድረስና ቴክኖሎጂ ከኢንዱስትሪው ፍላጎት በመነሳት ማፈላለግ፣
 መቅዳትና ማላመድ የሚችል ብቃቱ የተረጋገጠ የሰው ሃይል  የመገንባት ጥረት ሲደረግ
 ቆይቷል፡፡ ተቋማችን የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስፈፃም አካላትን ለማቋቋም፣ ስልጣንና ተግባራትን ለመወሰን ተሻሽሎ በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 17/2014 ተደራጅቷል፡፡
ሰይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ የክልሉን የሰይንስና ቴክኖሎጂ ፍላጎቶችን መለየት፣ጉዳዩ ከሚመለከታቸዉ ተዋንያን ጋር በመቀናጀትና በመወያየት የተለዩት ፍላጎቶች የሚሟሉበትን ሁኔታ ማመቻቸትና በክልሉ የቴክኖሎጂ ፓርክ  እንድያቋቁም የማድርግ ስልጣንና ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡ 
ዘመኑ የዲጂታል አለም ነው። የዲጂታል አለም ኢኖቬሽን ስነምህዳርን እንደ መሠረት አድርጎ ይጠቀማል።
ሁለሉም ዜጋ የዲጂታል ክህሎት ታጥቆ ለመጪው ዘመን እራሱን ማዘጋጀት እንዳለበት ተቋማችን በጽኑ ያምናል። የሲዳማ ክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ በክልላችን የተጀመረውን የዲጂታል ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ጠንካራ መሠረት እንዲኖረው በሰው ኃይል፣በአይሲቲ መሠረተ ልማት፣በአቅም ግንባታ እና የህግ ማዕቀፎች እንዲዘጋጁ እና መደላድል እንዲፈጠር በማድረግ አስቻይ ሁኔታ መፈጠር ዋነኛ አጀንዳ አድርጎ ይሰራል። እያንዳንዱ ዜጋ ያለልዩነት የዲጂታሉ አለም እድሎችን በእኩልነት መጠቀም አለበት።

Read more
ሳይንስ፣ቴክኖሎጂናኢኖቪሽን የመጪው ትውልድ ቋንቋ ነው!!

ዜናዎች

በሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን
#Sidaama: ክልሎች ጸጋዎቻቸውን በመለየት በሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን መሪነት ሃብትና ስራን መፍጠር ላይ በትኩረት እንዲሰሩ ተጠየቀ። === በሚንስቴር መስሪያቤቱ የተዘጋጀው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተጠሪ ተቋማትና የክልል አመራሮች የጋራ መድረክ የእቅድ ስምምነት በመፈራረም ተጠናቋል። ክቡር ሚንስትር ዶክተር በለጠ ሞላ በመድረኩ ማጠቃለያ፥ ተገኝተው የስራ መመሪያ ሰጥተዋል። እንደ ክቡር ሚንስትር ዶክተር በለጠ የአሁኑ ዓለም በሃብትና በስራ ፈጠራ እየተለወጠ
Photo
Critical Mass Cyber Security Requirement concept yitanno Istandarde aana INSAnni (Information Network Security Agency) daginno ogeeyye ejensete qajeelsha uyitu.
Photo
Sidaamu Dagoomu Qoqgowi Mootimma Sayinsenna Tekinoloojete Ejense 2016 M.D Mixo Woraddatenna Quchumu Gashshooti Ledo Halamate Looso Loosate Sheemate E'nanni Bare qixxeessitu. 2016 M.D mixo ejense woradunna quchumu gashshooti ledo halamatenni loosanno mixo titirshunni keente dirrisinno.

ፎቶ/ስዕል

k d d

 

ተልዕኮ

ለክልሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ጉልህ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ስራዎችን ለህብረተሰቡ በአግባቡ በማልማት፣ በመተግበርና በማስፋት ክልላዊ ብሎም አገራዊ የተወዳዳሪነት አቅምና በቴክኖሎጂ የዳበረ የአሰራር ስርዓት መፍጠር ነዉ፡፡

ራዕይ

በ2022 በክልላችን ውጤታማ የሆኑ የሳይንስና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂዎችን በፍጥነት የመማር፣ የማልማት፤ የማላመድ እና የመጠቀም አቅም ተገንብቶ ማየት

እሴቶች

በሳይንሳዊ ዕይታ መመራት

 የፈጠራ ሥራ ማበረታታት

 ሁል ጊዜ መማር

በቡድን መስራት

                 ጥራት ያለዉ አገለግሎት መስጠት

ዓላማ

ብቃትና ተነሳሽነት ያለዉ ከወቅታዊ ቴክኖሎጅ ለዉጥ ጋር ራሱን ማላመድ የሚችል የሰዉ ሀይል በመፍጠር እንድሁም ሀገርቱ የኢኖቨሽን ወይም የፈጠራ ምርምር ፣ለድጅታል ኢኮኖም አቅም በመፍጠር በቴክኖሎጅና በእዉቀት በመወዳደር፣በማሻሻል የሀገርቱን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገትን ማፍጠን ነዉ፡፡