Skip to main content

ተልዕኮ

ለክልሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ጉልህ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ስራዎችን ለህብረተሰቡ በአግባቡ በማልማት፣ በመተግበርና በማስፋት ክልላዊ ብሎም አገራዊ የተወዳዳሪነት አቅምና በቴክኖሎጂ የዳበረ የአሰራር ስርዓት መፍጠር ነዉ፡፡

           ራዕይ

2022 በክልላችን ውጤታማ የሆኑ የሳይንስና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂዎችን በፍጥነት የመማር፣ የማልማት፤ የማላመድ እና የመጠቀም አቅም ተገንብቶ ማየት

          እሴቶች

በጎ ህሊናና ቅን ልቦና፣ የስራ ፍቅርና ትጋት፣ ያልተገደበ አስተሳሰብና ምናባዊ ጉዞ፣ ለለውጥ በጋራ መስራት፤ ውጤታችንም ሆነ ውድቀታችን የጋራችን ነው፤ ችግር ፈቺነት፤ የማይረካ የመማር ጥማት፤ ለትውልድ የሚተላለፍ መሠረት፣ ቀልጣፋና ውጤታማ አሰራርና ቀጣይነት ያለው መሻሻል፣

        የተቋሙ ዓላማ

ብቃትና ተነሳሽነት ያለዉ ከወቅታዊ ቴክኖሎጅ ለዉጥ ጋር ራሱን ማላመድ የሚችል የሰዉ ሀይል በመፍጠር እንድሁም ሀገርቱ የኢኖቨሽን ወይም የፈጠራ ምርምር ፣ለድጅታል ኢኮኖም አቅም በመፍጠር በቴክኖሎጅና በእዉቀት በመወዳደር፣በማሻሻል የሀገርቱን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገትን ማፍጠን ነዉ፡፡