የግዥ ንብረትአ ስተዳደር ቡድን ዋና ዋና ተግባራት
- የስራ በጀት ዓመት የግዥ ፍለጎት ከስራ ክፍሎች መሰብሰብና ማዘጋጀት፡፡
- የግዥን ፍላጎትን ከበጀት ጋር በማገናዘብ የግዥ ዕቅድ ማዘጋጀት፡፡
- የዓመቱ የገበያ ጥናት ማከናወን
- የግልፅና የአከባቢ ጨረታ ማውጣት
- የጨረታ ሰነድ ማዘጋጀት
- የተለያዩ ውሎች ማዘጋጀት
- የንብረት ገቢና ወጪ ማድረግ
- ንብረቶችን በ70/ሀ እና70/ለ መዝገብ ላይ መመዝገብ
- ለቢሮው ንብረቶች ኮድ መስጠት
- ንብረት ቆጠራ ማድረግ
- ንብረት ማስተዳደር በመመሪያና በደንብ መሰረት ማስተዳደር
- አዲስ የተቋቋሙ ኮሌጆች ጨረታ ሂደቶችን መከታተልና መደገፍ
- ለተገልጋይ ምቹ ሁኔታ መፍጠር
የክፍያ ሂሳብ ሪፖርት ቡድን ዋና ዋና ተግባራት
- የበጀት አመቱን ዕቅድ ማዘጋጀት
- የመንግስትን ገንዘብን በመመሪያና በደንብ መሰረት ማስተዳደር
- የጥሬ ገንዘብ መርሃ ግብር ማዘጋጀት
- የተለያዩ ክፍያዎች ማዘጋጀት
- በየወሩ ከክለሉ ፋይናንስ ቢሮ ለመደበኛ እና ለካፒታል ስራ ማስኬጃ በአክሽን ፕላን መሰረት መጠየቅ
- የሰራተኛ ደመወዝ ቤወሩ ማዘጋጀትማዘጋጀት
- የክፍያ ሰነዶችን በ IBEX system መመዝገብ
- በየወሩ ሂሳብ ሪፖርት ማዘጋጀት
- የአደራ ሂሳቦችን ወደ ሚመለከተው ማስተላለፍ
- ለተገልጋይ ምቹ ሁኔታ መፍጠር
- ሰነዶችን ለሰነድ ክፍል ማስረከብ
ተገልጋይ አሞልቶ መቅረብያለበትቅድመ ሁኔታ
ሀ) የውስጥ ተገልጋይ
- ቀን ውሎ አበል ጥያቄ፡- የቀን ውሎ አበል ቅጽ በቢሮ በተዘጋጀው ፎርም ላይ የስራ ኃላፊን የት እና የቀን ብዛት በመሙላት አጸድቆ ማቅረብ፡፡
- የመኪና እና የሞተር ሳይክል ነዳጅ ጥያቄ፡-ነዳጅ ቅጽ በቢሮ በተዘጋጀው ፎርም ላይ የስራ ኃላፊን የት እንደሚሄዱ ቦታ በመግለጽ በመሙላት አጸድቆ እና በቢሮ አውቶ ባለሙያ የጌጅ ንባብ በማስሞላት ማቅረብ፡፡
- ከተለያዩ የስራ ዘርፎች የአቅም ግንባታ ስልጠና እንዲሁም የንቅናቄ መድረኮች ክፍያ በተመለከተ ፡- የጸደቀ በጀት መኖሩን ተረጋግጦ ፕሮፖዛል ማቅረብ ከስልጠናው ወይም ከንቅናቄው መድረክ ከአንድ ሳምንት በፊት
- የክፍያ ጥቄዎችን በተመለከተ፡-አንድ የውስጥ ተገልጋይ ቀደም ሲል የወሰደውን ክፍያ በማወዳደቅ ቀጣይ አገልግሎት ማግኘት ይችላል፡፡
- ሠራተኛ ደመወዝ በተመለከተ፡- ከሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የቢሮ ሰራተኛ የክረላንስ ሲመጣ የሰራተኛ ደመወዝ ይዘጋጃል፡፡
- የግዥን ጥያቄ በተመለከተ፡- በቢሮ ኃላፊዎች የጸደቀ ዝርዘር መግለጫ የያዘ ግዥ ጥያቄ ማቅረብ እንዲሁም በጀት መኖሩን ማረጋገጥ
- ንብረት ወጪን በተመለከተ፡- የንብረት ወጪ ቅጽ በኃላፊ ማጸደቅ
- ንብረት ገቢን በተመለከተ፡- በግዥ ኦፊሰር ህጋወነት ያለውን ደረሰኝ ይዞ መቅረብ ፤አሮጌ ንበረት ገቢ ንብረቱን ይዞ መገኘት
- የስልጠና ግዥዎችን በተመለከተ፡- የጸደቀ በጀት መኖሩን ተረጋግጦ ፕሮፖዛል ማቅረብ ከስልጠናው ወይም ከንቅናቄው መድረክ ከአንድ ሳምንት በፊት
ለ) የወጪ ተገልጋይ
- ክፍያዎችን በተመለከተ፡-አንድ ተገልጋይ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች ለምሳሌ የጨረታ ዕቃ(አገልግሎት) ግዥ ክፍያ የጨረታ ሰነዶች መሟላት ፤የንብረት ገቢ ደረሰኝ (ሞ/19)ይዞ መቅረብ፤የክፍያ ጥያቄ፤የውክልና ደብዳቤና መታወቂያ ኮፒ ማቅረብ
- የስልጠና ተሳታፊዎች ክፍያ ፡- ከመጡበት ቦታ ማንነታቸውንና የደመወዝ መጠን የስራ ድርሻ የሚገልጽ ደብዳቤ ሲያቀርቡ እና በስልጠናው ላይ በወቅቱ ሲሳተፋ
- የጨረታ ሰነድ ሽያጭ፡- ህጋዊ ንግድ ፍቃድ የታደሰ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን እንዲሁም የንግድ መለያ ቁጥር (Tin) ማቅረብ ፤የውክልና ደብዳቤ ማቅረብ፤የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ
- ተጫራቾች፡- የጨረታ ሰነድ ሞልተው ሲያቀርቡ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ
- የጨረታ አሸናፊን በተመለከተ፡- የአሸናፊነጽ ደብዳቤ ፈርመው መውሰድ ፤የውል ማስከበሪያ ማቅረብ ፤ውል መግባት ፤በውሉ መሰረት ንብረት ማቅረብ፤የቀረበውን ንብረት ማስገምገም፤ ንብረቱ በspecification መሰረት ከቀረበ ገቢ ማድረግ