የሳይንሰ እና ተክኖሎጂ አቅም ግንባታ ኣእምሮአዊ ንብረት እና ጨረራና የጥራት ቁጥጥር ዳይረክቶረት
- የክልላዊ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ ሰራዎችን ማመቻቸት ፡ ከሀገራዊ እና አለማቀፋዊ ተለዋዋጭነት ጋር ማጣጣም ።
- ክልላዊ የቴክኖሎጂ መረጃዎችን መሰብሰብ፣ ማደራጀት እና ማሰራጨት።
- የፓተንት፣ የኢንዱስትሪ ዲዛይን፣ የንግድ ምልክት እና የቅጂ መብትና ለተዛማጅ ጥያቄዎች የቴክኒክ ድጋፍ መስጠት፣ በክልል ዳታቤዝ ማደራጀት እና ከአእምሮአዊ ንብረት ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ለልማት ጥቅም ላይ ማዋል።
- ለተመራማሪዎች፣ ለኤክስፐርቶች ፣ለአጋሮች እና ለዲያስፖራ ማህበረሰብ በብሔራዊ እና ክልላዊ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለመሳተፍ ምቹ ሁኔታን መፍጠር።
- የቴክኖሎጂ እና ቴክኒካል ድጋፍ በመስጠት እና ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የሀገር በቀል ዕውቀትን ማስተዋወቅ እና ማሰጠበቅ ።
- ፈጠራንና እና ዲጂታላይዜሽን ለማዳበር በክልሉ ውስጥ የገንዘብ፣ የቁሳቁስ እና የቴክኒክ ድጋፍ ውጤታማ ስርጭትንና አጠቃቀምን ማረጋገጥ።
- ፈጠራን ለማስፋፋት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ካፌዎችን እና ክለቦችን በመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች እና በወጣቶች መዝናኛ ማዕከላት ማቋቋም።
- ለጀማሪዎች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ፓርኮችን፣ የእኒኩበሽን ማዕከላትን ማቋቋም።
- ክልላዊ፣ ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ ድጋፍን ለማስጠበቅ እና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ትብብርን ለማጎልበት መሰራት።
- ስለ ጥራት መሠረተ ልማት እና የተስማሚነት ግምገማ ለተጠቃሚዎችና ባለድርሻ አካላት መደበኛ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት።
- በማዕድን ማዉጫና(ፍለጋ) በሞባይል ማከሚያ ማዕከላት ላይ በተሰማሩ ተቋማት ላይ አደገኛ ጨረራና ኬሚካሎች አያያዝና ተያያዥ ስራዎችን መከታተልና መቆጣጠር።
- በክልላችን የሚመረቱ ምርቶች እና የሚሰጡ አገልግሎቶች ጥራትና ተወዳዳሪነት ማረጋገጥ።
- ለህክምና አገልግሎት የሚዉሉ ጨረር አመንጪ መሳሪያዎችን በመለየት፣ የአገልግሎት ደህንነት፣ ጥራትን ማረጋገጥ እና የተስማሚነት ምዘና፣ ቁጥጥር እና ግንዛበ የማሰጨበጥ ስራዎችን ማከናዎን።
- ከጨረር አመንጪ መሳሪያዎች ጋር የሚሰሩ ባለሙያዎች ብቁ የትምህርት ዝግጅት እንዳሏቸው ማረጋገጥ፣ የመሳሪያውን መመሪያ በመጠቀም ከመሣሪያው የሚመነጨውን የጨረር አይነት እና ባህሪ በመለየት እራሳቸውን፣ ህብረተሰቡን እና አካባቢውን የመጠበቅ እና የመረዳት ችሎታ/ግንዛቤ ማረጋገጥ።