Admin
Sat, 05/20/2023 - 15:34

#Sidaama:
ክልሎች ጸጋዎቻቸውን በመለየት በሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን መሪነት ሃብትና ስራን መፍጠር ላይ በትኩረት እንዲሰሩ ተጠየቀ።
===
በሚንስቴር መስሪያቤቱ የተዘጋጀው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተጠሪ ተቋማትና የክልል አመራሮች የጋራ መድረክ የእቅድ ስምምነት በመፈራረም ተጠናቋል።
ክቡር ሚንስትር ዶክተር በለጠ ሞላ በመድረኩ ማጠቃለያ፥ ተገኝተው የስራ መመሪያ ሰጥተዋል። እንደ ክቡር ሚንስትር ዶክተር በለጠ የአሁኑ ዓለም በሃብትና በስራ ፈጠራ እየተለወጠ የሚገኘው በሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ልማት፣ ምርምርና ዲጂታላይዜሽን ነው።
እንደ ሩቅ ምስራቅ አገራት ከተፈጥሮ ሃብት ባሻገር በርካታ ችግሮች ቢገጥሟቸውም ችግሮቻቸውን ተቋቁመው በዐለም ቀዳሚ መሆን የቻለ ኢኮኖሚ የገነቡት ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢኖቬሽን፥ ዲጂታላይዜሽንና ምርምርን በመጠቀማቸው ነው ሲሉ አውስተዋል።
እኛም እንደ አገር በርካታ ችግሮች ቢገጥሙንም በመላ ኢትዮጵያ በርካታ ጸጋዎች አሉን። በሁሉም ክልል ያለው ጸጋ ተለይቶ ትኩረት ተሰጥቶበት በሳይንስ በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽንና ዲጂታላይዜሽን ቢመራ ችግሮችን በመሻገር ስራና ሀብት መፍጠር ያስችላል ብለዋል።
ክልሎች ጸጋዎቻቸውን በመለየት በማወቅና በማቀድ በሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን መሪነት ሃብትና ስራን ለመፍጠር በትኩረት እንዲሰሩና የዘርፉም አመራር ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል።
Hawaasa Sidaama, Itophiya