የኤጀንሲዉ ስልጣንና ተግባር
1. የመገናኛና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎቶች ጥራታቸው፣ ደህንነታቸውና አስተማማኝነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን የሚያስችሉ ደረጃዎችን ይወስናል፣ ተግባራዊ መደረጋቸውን ያረጋግጣል፣
2. የመንግስት ተቋማት የመረጃ ስርዓትን ከመገንባትና ከማቀናጀት አንፃር የመንግስት የዶሜይን ስም ይደለድላል፣ አደራሻ ይመዘግባል ይቆጣጠራል፣
3. በክልል መንግስት ተቋማት መካከል ዘመናዊ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን መረብ መዘርጋቱን ይከታተላል፣ የሶፍትዌርና የሲስተም ልማት ሥራን ያከናውናል፣ እንዲከናወን ያደርጋል፣ ተገቢውን ድጋፍም ይሰጣል፣ ተግባራዊነቱን ይቆጣጠራል፡፡
4. በመንግስት ተቋማት መካከል የተቀናጀና ደህንነቱ የተጠበቀ የመረጃ ፍሰትና ልውውጥ እንዲኖር ድጋፍ ይሰጣል፤ በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋሉን ይከታተላል'
5. በየደረጃው ላሉ የመንግስት ተቋማትና የሕብረተሰብ ክፍሎች የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጥናት ዲዛይን ያዘጋጃል፣ ዘመናዊ የመረጃ ልውውጥ ፍላጎት ወይም ክፍተት የመለየት ስራ ያከናውናል፣ የመፍትሄ ሃሳብ ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፣
6. በክልሉ በየደረጃው ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ውስብስብና መለስተኛ ኢንፎርሜሽንና ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ-ልማት ይዘረጋል፣
7. በክልሉ የአስተዳደር እርከኖች የቪዲዮ ኮንፈረንሲንግ፣ የማህበረሰብ የመረጃ ማዕከላትን፣ የጥሪ ማዕከልና የማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያዎችን ያቋቁማል፣ ያስተዳድራል፣ ይቆጣጠራል፣
8. የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ የግል ሥራ ፈጠራ ማእከላትን ያቋቁማል፤
9. የክልሉን መረጃ መረብ ዝርጋታ እና ኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ሥራን ይከታተላል፣ ይደግፋል፣ ይቆጣጠራል፣ የሚለሙ ሶፍትዌሮችና አኘሊኬሽኖችን ደረጃ ይወስናል፤
10. በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ላይ የቴክኒክ የስልጠናና መሰል ድጋፎችን ያደርጋል፣ የብቃት ማረጋገጫና ፈቃድ ይሰጣል፣ ተግባራዊነቱንም ይቆጣጠራል፤
11. የክልሉ መንግስት የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን አጠቃቀም ይቆጣጠራል፣ እንዲጠገኑ ያደርጋል፣ ብልሽታቸው ከአቅም በላይ የሆኑትን ያሰውግዳል፣
12. ዓላማውን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል