Skip to main content

 

የእቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክተር

• መለስተኛ በጀት የሚያስተዳድሩ ተቋማትን እቅድ በማዘጋጀት፣

በማስተባበር፣በመምራት፣

አፈጻጸሙን በመከታተል እና በመገምገም የእቅድ ዝግጅት፣

ክትትልና ግምገማ ሥራዎች አፈጻጸም ውጤታማ እንዲሆን ማስቻል ነው ፡፡

2.2.ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት፣

• የሥራ ክፍሉን ዕቅድ ባለሙያዎችን አስተባብሮ ያዘጋጃል፣ይመራል፣ያስተተባብራል፣አፈጻጸሙን ይገመግማል፣

• ለሥራ ክፍሉ የሚያስፈልጉ የሰው ሀብት፣የገንዘብና የማቴሪያል እቅድ ያዘጋጃል፣ያስወስናል፣ ሲፈቀድም ሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፣

• የሥራ ክፍሉን ባለሙያዎች የአቅም ክፍተት በመለየት ክፍተቱን ለመሙላት የተለያየ ስልት በመንደፍ አቅማቸው እንዲገነባ ይሰራል፣

• የክፍሉን ሠራተኞች የሥራ አፈጻጸም ይገመግማል፣የሥራ አፈጻጸማቸውን ይመዝናል፣ ጠንካራ የሥራ አፈጻጸም የሚበረታታበትን ሁኔታ ያመቻቻል፡፡

• የተቋሙን የእቅድና የድርጊት መርሃ-ግብር ያዘጋጃልእንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ለግምገማ ያቀርባል፣ግብአቱ እንዲካተት በማድረግ ያጸድቃል፣ተፈጻሚነቱን ይከታተላል፣

• የመሥሪያቤቱ ዓመታዊና እስትራቴጂያዊ እቅድ ዝግጅት፣አፈጻጸም ክትትልና ግምገማ ሥራ የሚመራበትን ሥርዓት ይቀይሳል፤በአግባቡ ተግባራዊ መሆኑን ያረጋግጣል፣

• የተቋሙን ስትራቴጂክ ዕቅድ መነሻ በማድረግ ዓመታዊ እቅድ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ለጋራ ውይይት ያቀርባል የተሰጡ ጠቃሚ ግብአቶችን የእቅዱ አካል በማድረግ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣

• በተዘጋጀው የመረጃ አሰባሰብ ሥርዓት መሠረት የክትትልና ግምገማ መረጃዎች በአግባቡ መሰብሰባቸውንና መጠናቀራቸውን ያረጋግጣል፣

• የመሥሪያቤቱን የመካከለኛ እስትራቴጂክ እቅድ ዝግጅት ያስተባባራል፣ይመራል፣ያጠናቅራል፣ በኃላፊው ያጸድቃል፤ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤ይገመግማል፡፡

• የመሥሪያቤቱን የእቅድና በጀት አፈጻጸም ይከታተላል፣ይገመግማል፣በአፈጻጸም ላይ የታዩ ችግሮችን ይለያል፣ የመፍትሄ ሀሳብ ያቀርባል፣ ሲወሰን ለተግባራዊነቱ ይሰራል፣

• የፕሮግራም በጀት፣አመታዊ የፊዚካልና የበጀት እቅድ ዝግጅት ያስተባብራል፣ይመራል፣ለውይይት በማቅረብ ግብአቶችን አካቶ ያጸድቃል፣ተግባራዊነቱን ይከታተላል፣

• የበጀት ዝውውርና ተጨማሪ በጀት የማስፈቀድ ጥያቄን የማስተባበር ሥራን ይሰራል፣ተፈጻሚነቱን ይከታተላል፣

• የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣የተዘጋጀውን ሪፖርት ለተቋሙ የአመራር አካላት አቅርቦ በምክክርና ግምገማ መድረኮች ውይይት እንዲደረግባቸው ያደርጋል፣ ጠቃሚ ሀሳቦችን ያካትታል፣ሰነዱን አጸድቆ እንዲሰራጭ ያደርጋል፣

• በተቋሙ የሚጠኑ ችግር ፈቺ የሆኑ ጥናቶችን ያስተባብራል፣አንዲዘጋጁ ያደርጋል ተግባራዊነታቸውን ይከታተላል፣

• የፕሮጀክት ሀሳብ ያመነጫል፣ከሌሎች የሚመጡ የፕሮጀክት ሀሳቦችን ያስተባብራል ለውይይት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን እንዲለዩ ያደርጋል ተግባራዊ እንዲሆኑ ይከታተላል፣

• የተቋሙን የስትራቴጂክ፣የመደበኛ እቅዶችና ፕሮጀክቶች አፈጻጸም የተገኘውን ፋይዳ ለመገምገም የሚያስችል መስፈርት በማዘጋጀት እንዲገመገም ያደርጋል፣የተገኘውን ውጤት ለኃላፊው ያቀርባል፡፡