አቶ ተፈራ ባራሳ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ጀነራል ዳይሬክተር መልዕክት
ለአንድ ሀገር እድገት የኢኖቬሽናል ቴክኖሎጂ ሚና በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ ስለሆነም ቴክኖሎጂ መነሻ ያደረጉ የኢኖቬሽን ልማት ላይ ጠንክረን መስራት ይጠበቅበረናል፡፡
ከዘረፉ ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የባለድረሻ አካላትን ለይተን እየሰራን ቆይተናል፡፡ በመሆኑም ዉጥኑን ከግብ ለማድረስና ቴክኖሎጂ ከኢንዱስትሪው ፍላጎት በመነሳት ማፈላለግ፣
መቅዳትና ማላመድ የሚችል ብቃቱ የተረጋገጠ የሰው ሃይል የመገንባት ጥረት ሲደረግ ቆይቷል፡፡ ተቋማችን የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስፈፃም አካላትን ለማቋቋም፣ ስልጣንና ተግባራትን ለመወሰን ተሻሽሎ በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 17/2014 ተደራጅቷል፡፡
ሰይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ የክልሉን የሰይንስና ቴክኖሎጂ ፍላጎቶችን መለየት፣ጉዳዩ ከሚመለከታቸዉ ተዋንያን ጋር በመቀናጀትና በመወያየት የተለዩት ፍላጎቶች የሚሟሉበትን ሁኔታ ማመቻቸትና በክልሉ የቴክኖሎጂ ፓርክ እንድያቋቁም የማድርግ ስልጣንና ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡
ዘመኑ የዲጂታል አለም ነው። የዲጂታል አለም ኢኖቬሽን ስነምህዳርን እንደ መሠረት አድርጎ ይጠቀማል።
ሁለሉም ዜጋ የዲጂታል ክህሎት ታጥቆ ለመጪው ዘመን እራሱን ማዘጋጀት እንዳለበት ተቋማችን በጽኑ ያምናል። የሲዳማ ክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ በክልላችን የተጀመረውን የዲጂታል ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ጠንካራ መሠረት እንዲኖረው በሰው ኃይል፣በአይሲቲ መሠረተ ልማት፣በአቅም ግንባታ እና የህግ ማዕቀፎች እንዲዘጋጁ እና መደላድል እንዲፈጠር በማድረግ አስቻይ ሁኔታ መፈጠር ዋነኛ አጀንዳ አድርጎ ይሰራል። እያንዳንዱ ዜጋ ያለልዩነት የዲጂታሉ አለም እድሎችን በእኩልነት መጠቀም አለበት።