Skip to main content

                 የሚሰጡ አገልግሎቶች፦

  • በፈጠራ ስራ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃ ተጠቃሚ የሆነ ማህበረሰብ እንዲፈጠር ይደረጋል፤
  • ተገልጋዮች ህጋዊ እውቅናና ጥበቃ የሚያገኙበትን የአእምሮ ንብረት ተግባራዊ በማድረግ እያጋጠማቸው ያለውን ችግሮች እንዲፈታላቸው ይደረጋል፤
  • የአእምሯዊ ንብረት ህጋዊ ዕዉቅናና ጥበቃ ውሳኔ አፈጻጸምን ይከታተላል
  • ህጋዊ ዕዉቅና የተሰጣቸዉን የፈጠራ ስራዎችን ጥቅም ላይ እንድዉል የሚያስችል የማስተዋወቅ ስራ በሚዲያ፣ በበራሪ ወረቀት፣ በመረጃ መረብ፣ በኢግዚቢሽንና ባዛር ይሠራል፡፡
  • ወቅታዊና ቀልጣፋ የሆነ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃ አገልግሎት ይሰጣል፡፡
  • ለአእምሯዊ ንብረትና ለፈጠራ ስራ ዉጤቶች ህጋዊ ጥበቃና ዕዉቅና ይሰጣል፡፡
  • በክልላችን የሚካሄዱ የአእምሯዊ ንብረትና የፈጠራ ስራዎች ተናበውና ተመጋግበው እንዲሄዱ የሚያስችል አሰራር እንዲዘረጋ ይሰራል
  •  እውቅና ያገኙ የአእምሮ ንብረት ውጤቶች ወደ ማህበራዊ ጥቅም እንዲለወጡ ያደርጋል
  •  ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የአካል ጉዳተኞች፣ ሴቶች በአምሯዊ ንብረትና ፈጠራ ስራዎች ያላቸው ተሳትፎና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ስርአት እንዲፈጠር ይሰራል
  • ከባለድርሻ አካላት ጋር የምርምር የትስስር ፎረም/ምክር ቤት አንዲቋቋም ያደርጋል፤ ያስተባብራል፣ ይመራል፤
  • ምርምር ለማካሄድ ፕሮፖዛል እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ይገመግማል፤ ያፀድቃል፤ ለምርምሩ በጀት እንዲመደብ ያደርጋል፤ይከታተላል፤
  • የማህበረሰቡን ችግር ሊፈቱ የሚችሉ ሳይንሳዊ ምርምሮች እንዲካሄዱና የተገኙት የምርምር ውጤቶች እንዲሸጋገሩ ያደርጋል፤ያስተባብራል፣ ይመራል፣ ይደግፋል፤
  • ኢንዱስትሪዎች፤ አርሶአደሮች፤ ኢንተርፕራይዞች፤ የምርት ጥራትና ምርታማነታቸውን በማሻሻል ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን ለማቅረብ የሚያስችል የምርምርና ኢኖቬሽን ስራን ይመራል፣ ይደግፋል፤
  • የፖሊሲ ሀሳቦችን ያመነጫል፣ ኢንዱስትሪዎችና ኢንተርፕራይዞች ሊከተሉት የሚገባ የሳይንስና ቴክኖሎጂ የመቅዳት ስትራቴጂዎችን ይለያል፣ ያወጣል፣ ይገመግማል፣
  • ለምርምር ውጤቶች የህግ ማዕቀፎችን ማዘጋጀት ካስፈለገ እንዲዘጋጅ ሀሳብ ያቀርባል፣ ያዘጋጃል፣ ይገመግማል፣ ተግባራዊነታቸውን ይከታተላል፤
  • የክልሉን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት እንዲካሄድና የተደራጀ መረጃ እንዲኖር ያስተባብራል፤ ይደግፋል፤
  • በጥናት የታዩ ክፍተቶችን መሰረት በማድረግ የህግ ማዕቀፎችን ማዘጋጀት ካስፈለገ እንዲዘጋጅ ሀሳብ ያቀርባል፣ ያዘጋጃል፣ ይገመግማል፣ ተግባራዊነታቸውን ይከታተላል፤
  • የተሸጋገሩ ቴክኖሎጂዎችና የምርምር ውጤቶች በህብረተሰቡ ውስጥ ያመጡትን ፋይዳ በዳሰሳ ጥናት የመለየትና ግብረመልስ የመስጠት ስራን ይመራል፤ ያስተባብራል፤
  • ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት፤
  • ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምርና ፈጠራ ስራዎች የፋይናንስ፤ ማቴሪያልና ቴክኒክ ድጋፍ ማድረግ፤
  • በት/ቤቶች የሳይንስ ሳምንታት እንዲከበሩ ማድረግ፣
  • ድጋፍ በማፈላለግ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበባትን በየትምህርት ቤቱ ማቋቋም፤
  • በየተቋማቱ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና የኢኖቬሽን ስራዎችን ውጤታማ የሚያደርጉ የምርምር ክፍሎች የማቋቋም፤
  • የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፓርኮች እንዲቋቋሙ ማድረግ
  • የሳይንስና ቴክኖሎጂ የአሰራር ስርአት መዘርጋት፤
  • የሳይንስና ቴክኖሎጂ የሰው ኃይል ፍላጎትን በጥናት በመለየት አቅም የመገንባት ሥራ መስራት በዳይሬክቶሬቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ናቸው፡፡
  • የጨረራ አመንጪ መሳሪያዎችን በመለየትና በመከታተል ህብረተሰቡ ካስከፊ ጉዳት  እንዲጠበቅ ይደረጋል፤
  • በአገልግሎት ላይ እየዋሉ ያሉ መሳሪያዎች የካሊብሬሽን ስራ ማከናወናቸዉን የማረጋገጥ ሥራ ይሠራል፤
  • ምርቶችና አገልግሎቶች የጥራት ደረጃቸውን ስለማሟላታቸው ከሚመለከተዉ አከላት ጋር በትብብር በመስራት አግባብ ያለው ሙያዊ አገልግሎት መስጠቱን ያረጋግጣል፣
  • በጥራት እና ደረጃዎች ዙሪያ የተለያዩ የአህዝቦት ስራዎች እንዲካሄዱ ያደረጋል፣
  • የክልሉ ህብረተሰብ ከባህላዊ መመዘኛዎች ወደ ዘመናዊ አለካክ እንዲለወጥ ትኩረት ተሰጥቶ ይሠራል፡፡
  • የህክምና ተቋመት፤በኢንዱስትሪዎች፣ በዩኒቨርሲቲዎች፣ቤተሙከራዎችና በምርምር ተቋማት መካከል ጠንካራ ትስስርና ትብብር እንዲፈጠር ሁኔታዎችን በማመቻቸት የጨረራ ኢንስፔክሽንና የጥራት መሠረተ ልማት ስራ በትብብር እንዲሰራ ይደረጋል 
  • በሬዲዮ አክቲቭ ኬሚካል የሚገለገሉ ቤተሙከራዎች፣ምርምር ማዕከላት፣ህክምና ማዕከላት እና ኢንዱስትሪዎችን ለመከታተል የሚያግዙ መሳሪያዎች እንዲጠቀሙ/እንዲያስገቡ በማድረግ ብክለትን ማስወገድ እና ብክለት በሚያጋጥምበት ጊዜ አስቸኳይ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል አሰሪር እንዲሰፍን ይደረጋል፡፡
  • የጨረር አመንጪ መሳሪያዎች እና የሬዲዮ አክቲቭ ቆሻሻ ጨረር አመንጪ ኬሚካሎች ክልላዊ ዳታ ቤዝ እንዲኖር ይደረጋል፡፡
  • የሥነ-ልክና አክሪዲቴሽን ሥራ ከባለድርሻ አካላት ጋር በተጠናከረ መልኩ ይሠራል፡፡
  • በክልሉ የሚመረቱ ምርቶችና የሚሰጡ አገልግሎቶች የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁና የተስማሚነት ምዘና በማድረግ ተወዳዳሪነታቸው የተረጋገጠ እንዲሆን ይደርጋል
  • የጨረራ አመንጪ መሣሪያዎች ጥቅምና ጉዳት የተስማሚነት ምዘና የጥራት ማረጋገጫ ጠቀሜታ ለተገልጋዮችና ባለድርሻ አካላት ተከታታይ የሆኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች ይሠጣሉ፡፡
  • በፈቃድ መስጠት እና ኢንስፔክሽን ወቅት ለሚሰጥ አገልግሎት ከክፍያ ነጻ በማድረግ ከጨረር ጋር የተያያዘ ቴክኖሎጂ በሰፊው ወደ ክልላችን እንዲገባ ማድረግ እና ጨረር ነክ ኢንዱስትሪዎችን ማበረታታት ይገባል፡፡
  • ህብረተሰቡ በተደጋጋሚ የሚገለገልባቸው መሳሪያዎች ለምሳሌ ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ማይክሮዌቭ ምድጃ፣ የጀርም እና ፀረ ባክቴሪያ መሳሪያ፣ የሚመለከቱ አዲስ የምርምር ውጤት ተግባራዊ ያደረገ ወቅታዊ ማስረጃ/መረጃ በሚወጣበት ጊዜ ክትትል በማካሄድ መረጃውን ለህዝብ እንዲደረስ በማድረግ  ህብረተሰቡ ሳያስበው በድንገተኛ አደጋ እንዳይወድቅ ማድረግ፣
  • በዘመናዊ ሶፍትዌር እና ዳታ ቤዝ የተጠናከረ የቁጥጥር እና ኢንስፔክሽን ስርአት በመጠቀም ኢንስፔክተሮች ቀልጣፋ አገልግሎት የሚሰጡበት ዘመናዊ አሰራር ይፈጠራል፡፡
  • ፈቃድ በሚሰጥበት ወቅት ለሚሰጠው የኢንስፔክሽን አገልግሎት የሚጠየቅ ክፍያ፡-የመሳሪያዎች ብዛት፣የመሳሪያ አይነት፣የቦታ ርቀት፣የአካባቢ አየር ፀባይ፣ለስራው የሚመደቡ ባለሙያዎች የስራ ሂደቱን መሰረት ያደረገ እንዲሆን በማድረግ የወጪ ፍትሃዊ ክፍፍል እንዲካሄድ በማድረግ ከመንግስት ካዝና አላስፈላጊ ወጪ እንዲይወጣ ይደረጋል፣፡