የኢኮቴ የግል ሰራተኞች መገናኛ እና መረጃ ማዕከል አስተዳደር ዳይረክቶሬት
የሚሰጡ አገልግሎቶች
- አዳዲስ ኢንኩቤቶችን ይመለምላል መሠረታዊ የኢንተርፐርነርሺፕ፤ የቢዝነስ እቅድ አዘገጃጀትና የሂሳብ አያያዝ ሥልጠናዎችንና የአቅም ግንባታ ድጋፍ ይሰጣል
- የእያንዳንዱን ኢንኩቤት ድርጅት የቢዝነስ ዕቅድ ይገመግማል ፣ግብረመልስ ይሰጣል፣ ያደራጃል፣ ያበቃል፡፡
- በማዕከል ውስጥ ያሉ ንብረቶችን ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ለኢንኩቤቶች ያከፋፍላል የመስሪያ ቦታን በኪራይ ይሰጣል፡፡
- በመደበኛ ሁኔታ የኮቺንግና ሞንተሪንግ አገልግሎት ለኢንኩቤቶች ይሰጣል
- በየወቅቱ የኢንኩቤቶች የሥራ አፈጻጸምን ይገመግማል፣ አስተያየት ይሰጣል፣ እርምጃ ይወስዳል፣ ደካማና ጠንካራዎችን ይለያል፡፡
- የገበያ ትስስር ይፈጥራል፣ የተገኙ የገበያ ዕድሎችን በውድድር ወይም ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ኢንኩቤቶች እንዲተቀሙ ያደርጋል፡፡
- ኢንኩቤቲዎች በመንግስት ደንብ መሰረት በህግ እንዲቋቋሙ ያደርጋል
- የኢንኩቤቶችን ክፍተት በመለየት አስፈላጊውን ሥልጠናና የአቅም ግንባታ ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡ብቁ የሆኑ ኢንኩቤት ድርጅቶችን በመለየት ያስመርቃል በገበያ ውስጥ ገብተው ተወዳዳሪና ብቁ ባለሃብት እንዲሆኑ ያግዛል፡